Addis Ababa, October 16, 2018
ጠ/ሚ ዶክተር አብይ እጩ የካቢኔ አባላትን ለምክር ቤቱ አቅርበው ያስፀድቃሉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 6፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አዲስ በቀረበው የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው ረቂቅ አዋጅ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ እጩ የካቢኔ አባላትን ለሀዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው ያስፀድቃሉ።
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት እያካሄደ ባለው 2ኛ መደበኛ ስብሰባው የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በረቂቅ አዋጁ መሰረትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ 19ኙን የሚኒስትር መስሪያ ቤቶች ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው እንደሚያፀድቁ ይጠበቃል።
በዚህም መሰረት፦
1. የሰላም ሚኒስቴር
2. የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር
3. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
4. የገንዘብ ሚኒስቴር
5. ጠቅላይ አቃቤ ህግ
6. የግብርና ሚኒስቴር
7. የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
8. የገቢዎች ሚኒስቴር
9. የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
10. የትራንስፖርት ሚኒስቴር
11. የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር
12. የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር
13. የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር
14. የትምህርት ሚኒስቴር
15. የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
16. የጤና ሚኒስቴር
17. የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር
18. ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
19. የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር
1. የሰላም ሚኒስቴር
2. የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር
3. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
4. የገንዘብ ሚኒስቴር
5. ጠቅላይ አቃቤ ህግ
6. የግብርና ሚኒስቴር
7. የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር
8. የገቢዎች ሚኒስቴር
9. የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
10. የትራንስፖርት ሚኒስቴር
11. የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር
12. የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር
13. የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር
14. የትምህርት ሚኒስቴር
15. የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
16. የጤና ሚኒስቴር
17. የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር
18. ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር
19. የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር
በረቂቅ አዋጁ መሰረት ከአሁን በፊት የነበሩ እና ከዚህ በኋላ የማይቀጥሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች
1. የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር ሚኒስቴር - በሰላም ሚኒስቴር ስር የተጠቃለለ
2. የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት - በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሰክሬታሪያት የሚተካ
3. የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር - የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የተጠቃለሉ
4. የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር- በአንድ ላይ የተዋሃዱ
5. የከተማ እና ቤቶች ልማት ሚኒስቴር - ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ጋር የተዋሃዱ
1. የፌደራል ጉዳዮችና አርብቶ አደር ሚኒስቴር - በሰላም ሚኒስቴር ስር የተጠቃለለ
2. የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት - በጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሰክሬታሪያት የሚተካ
3. የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር - የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር የተጠቃለሉ
4. የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር- በአንድ ላይ የተዋሃዱ
5. የከተማ እና ቤቶች ልማት ሚኒስቴር - ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ጋር የተዋሃዱ
ምክር ቤቱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ እንደገና ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸውም መንግስት ባለፉት ጥቂት ወራት ሲሰራው በነበረው የማሻሻያ ስራ ሰላምን ማረጋገጥ፣ ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖር፣ ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዲጠበቁ፣ ህገ መንግስቱ እና የህግ የበላይነት እንዲከበር እና ከሌብነት የፀዳ አሰራር እንዲኖር የህዝቡ ፍላጎት መሆኑን ተረድተናል ብለዋል።
ለዚህም ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ የመንግስት ተቋማትን በአዲስ መልክ እንዲደራጁ እንዲሁም ፈጣን ምላሽ በሚሰጥ መልኩ የካቢኔ አባላትን ቁጥር ወደ 20 ዝቅ እንዲል መወሰኑን አንስተዋል።
ረቂቅ አዋጁ የአስፈፃሚ አካላትን ማጠናከር የሚችል መሆኑንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ያስረዱት።
በቀጣይም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ፍርድ ቤቶች፣ የዴሞክራሲ ተቋማት፣ የምርጫ ቦርድ፣ የህዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም እና ሌሎች ተቋማትም ራሳቸውን በመፈተሽ እንደ አዲስ እንደሚደራጁ አስረድተዋል።
Source: FBC
PM Dr. Abiy Ahmed will present the members of the Cabinet to the House
The Prime Minister has presented the Candidate members to
the House of People's Representatives on a draft bill to determine the powers
and duties of the newly formed bodies.
The House of Peoples' Representatives is expected to discuss
and approve the draft Proclamation to revise its mandate to determine the
powers and duties of the Executive Organs at its 2nd regular meeting today.
On the basis of the Draft Law, Prime Minister Dr. Abiy Ahmed
will be expected to approve the 19th Ministerial Council for the House of
Peoples' Representatives.
Accordingly,
1. Ministry of Peace
2. Ministry of National Defense
3. Ministry of Foreign Affairs
4. Ministry of Finance
5. General Prosecutor
6. Ministry of Agriculture
7. Ministry of Trade and Industry
Ministry of Revenue
9. Ministry of Innovations and Technology
Ministry of Transport
11. Ministry of Urban Development and Construction
12. Ministry of Water Resources and Energy
13. Ministry of Mines and Energy
Ministry of Education
15. Ministry of Science and Higher Education
Ministry of Health
Ministry of Women, Children and Youth
18. Ministry of Labor and Social Affairs
19. Ministry of Culture and Tourism
According to the Draft Act, the previous and future
ministries
1. Ministry of Federal Affairs and Pastoral Affairs - Under
the Ministry of Peace
2. Government Communication Affairs Office - Replacing Press
Secretariat with the Prime Minister's Office
Ministry of Youth and Sport - Ministry of Women, Children
and Youth
4. Ministry of Trade and Industry - Consolidated
5. Ministry of Urban Development and Housing - Ministry of
Construction
The House of Peoples' Representatives of the Federal
Democratic Republic of Ethiopia, Dr. Abiy Ahmed, discussed the draft
proclamation to determine the mandate and functions of executive bodies.
He noted that the Ethiopian government is keen to ensure
peace, ensure equitable wealth distribution, protect human and democratic
rights, improve the constitution and the rule of law, and be free of devious
behavior.
In this way, the government has decided to reorganize the
government institutions in a cost-efficient manner and to reduce the number of
members to 20, with a rapid response.
Prime Minister Dr. Abiy Ahmed said that the draft law could
further strengthen the executive branch.
In addition, the House of People's Representatives, the
Courts, the Democratic Institutions, the Election Board, the Ombudsman
Institution and other institutions will be reorganized, he added.
No comments:
Post a Comment